Find Posts By Topic

ስለ COVID-19 እና “የመንግስትድጎማዎች” ጥያቄዎች እና መልሶች

English-version of this page here.

በዚህ ገጽ ውስጥ ያለው መረጃ የሕግ ምክር አይደለም። ከዚህ ይልቅ፣ ከዚህ በታች ያለው ይዘት በሙሉ ለጠቅላላ መረጃ ዓላማዎች ብቻ የሚውል ነው።

Image of a Coronavirus

ይህ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የጥቄዎች እና መልሶች (FAQ) የመረጃ መምሪያ የ public charge (ሕዝባዊ ክፍያ) ጉዳይ በዚህ የ COVID-19 (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ወቅት የጤና እንክብካቤና ሌሎች አገልግሎቶችን የማግኘት ችሎታቸው ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለሚፈልጉ ስደተኞች የተዘጋጀ ነው። የ Office of Immigrant and Refugee Affairs (የኢሚግራንትና ስደተኞች ጉዳይ ቢሮ) አዳዲስ ነገሮች ሲፈጠሩ ይህን ድረ ገጽ በአድስ መረጃ ማሻሻሉን ይቀጥላል።

ልዩ ምስጋና ለ El Comite (ኮሚቴው) እና Northwest Immigrant Rights Project (ለሰሜን ምዕራብ የኢሚግራንት መብቶች ፕሮጄክት) ይህን መረጃ ለማጠናቀቅ ላደረጉት ድጋፍ።


ወደ ጥያቄው ያምሩ፡-

  1. የ COVID-19 (ኮቪድ-19) ኢንፌክሽን እንዳለብኝ እጠራጠራለሁ፣ ምን ላድርግ?
  2. ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታ መረጃን ለ U.S. Immigration and Customs Enforcement (ICE፣ የዩኤስ ኢሚግሬሽንና የጉምሩክ አስከባሪ) ያጋራሉ?
  3. ለ COVID-19 (ኮቪድ-19) መመርመር ወይም የበጎ አድራጎት እርዳታ ወይም በሆስፒታል ወይም ክሊኒክ ውስጥ በቅናሽ ዋጋ አገልግሎት ማግኘት በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዬ ላይ ተጽእኖ ያሳድርብኛል?
  4. የበጎ አድራጎት ወይም በቅናሽ ዋጋ እንክብካቤ የሚሰጡና እኔ ልሄድባቸው የምችላቸው የአካባቢ ማህበረሰብ ክሊኒኮች ወይም ሆስፒታሎች የትኞቹ ናቸው?
  5. እኔ ሰነድ አልባ ነኝ፣ በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት የፋይናንስ ጉዳት ደርሶብኛል። ሰነዶቼን ሳላሳይ ላመለክትና ላገኛቸው የምችላቸው ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች የትኞቹ ናቸው?
  6. በወረርሽኙ ምክንያት ስራ አጥ ሆኛለሁ። ለስራ አጥነት ኢንሹራንስ ብቁ ነኝ?
  7. የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅም መቀበል በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዬ ላይ ተጽእኖ ያሳድርብኛል?
  8. እኔ በመታመሜ ወይም የቤተሰቤ አባል በመታመሙ ወይም በዶክተር መታየት ስላለበት ከስራ እየቀረሁ ነው። ለ Paid Sick & Safe Time (PSST፣ የህመም እና ደህንነት ዕረፍት ጊዜ ክፍያ ለማግኘት) ብቁ ነኝ?
  9. እኔ በመታመሜ ወይም የቤተሰቤ አባል በመታመሙ ወይም በዶክተር መታየት ስላለበት ከስራ እየቀረሁ ነው። ለ Washington ግዛት Paid Family and Medical Leave ብቁ ነኝ?
  10. ከሥራ የመቀነስ አደጋ ላይ ካለሁ ወይም እኔ ወይም ወዳጄ በመታመሙ ምክንያት ማቆም ካለብኝስ?
  11. የአነስተኛ ንግድ ባለቤት ስሆን በወረርሽኙ ምክንያት የንግድ መቀዛቀዝ እያጋጠመኝ ነው። ለገንዘብ እርዳታ ብቁ ነኝ?
  12. ለ Seattle ከተማ አነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈቃድ ወይም ለፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር አደጋ ብድር ማመልከት በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዬ ላይ ተጽእኖ ያሳድርብኛል?
  13. ለበለጠ መረጃ መርጃዎች፦

 

1. የ COVID-19 (ኮቪድ-19) ኢንፌክሽን እንዳለብኝ እጠራጠራለሁ፣ ምን ላድርግ?

የ COVID-19 (ኮቪድ -19) ምልክቶች ካሉብዎ ወይም ጥያቄዎች ካሉዎ፣ ስልክ መደወል ይችላሉ፡-

  • የኪንግ ካዉንቲ የኖቬል ኮሮናቫይረስ ጥሪ ማእከል (206) 477-3977። ይህ የአገልግሎት መስመር ከጧት 8 ስዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት በየእለቱ ክፍት ነዉ።
  • የዋሽንግተን ስቴት የኖቬል ኮሮናቫይረስ ጥሪ ማእከል (800) 525-0127 ና #ን ይጫኑ። ይህ የአገልግሎት መስመር ከጧት 6 ስዓት እስካ ሌሊት 10 ሰዓት በየእለቱ ክፍት ነዉ።

ኦፕሬተሮቹ ከሶስተኛ ወገን አስተርጓሚ ጋር ማገናኘት ይችላሉ። የየትኛው ቋንቋ አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ በእንግሊዘኛ መንገር መቻል አለብዎት። ለረጅም ጊዜ መስመር ላይ ልጠብቁ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ ወደሚከተለው ይሂዱ: – Public Health – Seattle & King County

 

2. ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታ መረጃን ለ U.S. Immigration and Customs Enforcement (ICE፣ የዩኤስ ኢሚግሬሽንና የጉምሩክ አስከባሪ) ያጋራሉ?

የለም። Health Insurance Portability and Accountability Act (HIPAA፣ የጤና ኢንሹራንስ ተዘዋዋሪነትና ተጠያቂነት ደንብ) በመባል የሚታወቀው የፌዴራል ሕግ የታካሚ መረጃ ያለታካሚው ፈቃድ ጥቅም ላይ እንዳይውል ወይም እንዳይገለጽ አጠቃላይ ክልከላ ያደርጋል። በተጨማሪም፣ የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች የአንድን ታካሚ የኢሚግሬሽን ሁኔታ በተመለከተ ለፌዴራል የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ሪፖርት እንዲያደርጉ ሕጋዊ ግዴታ የለባቸውም።

 

3. ለ COVID-19 (ኮቪድ-19) መመርመር ወይም የበጎ አድራጎት እርዳታ ወይም በሆስፒታል ወይም ክሊኒክ ውስጥ በቅናሽ ዋጋ አገልግሎት ማግኘት በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዬ ላይ ተጽእኖ ያሳድርብኛል?

የለም። ለ COVID-19 (ኮቪድ-19) መመርመርና የበጎ አድራጎት ወይም ቅናሽ ዋጋ ያለው የሕክምና እንክብካቤ ማግኘት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዎ ላይ ተጽእኖ አያሳድርም። በአካባቢው ያሉ በቅናሽ ዋጋ የሕክምና እንክብካቤ የሚሰጡ ፕሮግራሞች አሁን ባለው የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት እንደ ሕዝባዊ ጥቅም አልተዘረዘሩም። U.S. Citizenship and Immigration Services (የዩኤስ የዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎቶች) ይህን መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ መግለጫውም ከ COVID-19 (ኮቪድ-19) ጋር የተያያዙ “የሕክምና ወይም የመከላከያ አገልግሎቶች” ለሕዝባዊ ክፍያ ዓላማዎች ታሳቢ እንደማይደረጉ ያብራራል።

የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ የሚከተሉትን የሕዝባዊ ድጋፍ ዓይነቶች ብቻ በትንተናው ውስጥ ታሳቢ ያደርጋል፡-

  • የፌዴራልና የግዛት የግለሰብ የገቢ ሁኔታን ከግምት ያስገባ የጥሬ ገንዘብ ጥቅማ ጥቅሞች፣ ለምሳሌ፡ SSI (Supplemental Security Income (የተጨማሪ ዋስትና ገቢ)), TANF (Temporary Assistance to Needy Families (ለችግረኛ ቤተሰቦች የሚሰጥ ጊዜያዊ ድጋፍ)) እና GAU (General Assistance Unemployable (ለአካል ጉዳተኛ ስራ አጦች የሚሰጥ አጠቃላይ ድጋፍ)።
  • በመንግስት ስፖንሰር የሚደረጉ ዘላቂ ተቋማዊ እንክብካቤ፣ ለምሳሌ አብዛኛውን ጊዜ በ Medicaid (ሜዲኬይድ) የሚሸፈን መንከባከቢያ ማዕከል ወይም የአእምሮ ጤና ተቋም።
  • Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP፣ የምግብ ንጥረ ነገር ማሟያ ድጋፍ መርሃ ግብር)፣ ቀድሞ “Food Stamps (የምግብ ማኅተሞች)” ይባሉ ነበር።
  • የሚደጎም የቤት ኪራይ፣ ለምሳሌ፡- ሀ) የፌዴራል የክራይ ድጋፍ፣ ለ) Section 8 housing vouchers (ክፍል 8 የቤት ደረሰኞች) እና ሐ) ማንኛውም ከፕሮጄክት ተኮር Section 8 (ክፍል 8) ድጋፍ የሚያገኝ የቤት አገልግሎት።

ስለ ሕዝባዊ ክፍያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ይህን ይጎብኙ፡- seattle.gov/OIRA/publiccharge

 

4. የበጎ አድራጎት ወይም በቅናሽ ዋጋ እንክብካቤ የሚሰጡና እኔ ልሄድባቸው የምችላቸው የአካባቢ ማህበረሰብ ክሊኒኮች ወይም ሆስፒታሎች የትኞቹ ናቸው?

መጋቢት 5 ቀን፣ Washington State Insurance Commissioner (የዋሽንግተን ግዛት የኢንሹራንስ ኮሚሽነር) የኢንሹራስ ድርጅቶች ለ COVID-19 (ኮቪድ-19) ምርመራ ለማድረግ የጣምራ ክፍያዎችና ተቀናናሾችን እንዲያስቀሩ የሚያስገድድ መሆኑን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም፣ Washington State Health Care Authority (HCA፣ የዋሽንግተን ግዛት የጤና እንክብካቤ ባለስልጣን)በአሁኑ ጊዜ ሰነድ አልባ አዋቂ ሰዎች ለ COVID-19 (ኮቪድ-19) መመርመር ካስፈለጋቸው ለ Alien Emergency Medical (AEM፣ የውጭ ዜጎች አጣዳፊ ሕክምና) እንዲያመለክቱ ይፈቅዳል። ግለሰቦች ወደ www.washingtonconnection.org በመግባት ወይም Application for Long-Term Care/Aged, Blind, Disabled Coverage (የዘላቂ እንክብካቤ/የአረጋውያን፣ ዓይነ ስውራን፣ አካል ጉዳተኞች ሽፋን ማመልከቻ (HCA 18-005) በመሙላት ማመልከት ይችላሉ። ማመልከቻውን ከ Health Care Authority ድረ ገጽ ማውረድ ይችላሉ። ጥያቄዎች ካሉዎት፣ ለ HCA በስልክ ቁጥር 1-800-562-3022 ደውለው አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ።

Washington Healthcare Access Alliance (የዋሽንግተን የጤና እንክብካቤ ተደራሽነት ሕብረት) በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ በነጻና በበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮችን በካውንቲ ደረጃ ዝርዝራቸውን አስቀምጧል፡- wahealthcareaccessalliance.org/free-clinics

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ክሊኒኮች ለ Seattle አካባቢ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን የዋጋ ቅናሽ ያሉባቸው የእንክብካቤ ፕሮግራሞች አላቸው።

 

5. እኔ ሰነድ አልባ ነኝ፣ በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት የፋይናንስ ጉዳት ደርሶብኛል። ሰነዶቼን ሳላሳይ ላመለክትና ላገኛቸው የምችላቸው ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች የትኞቹ ናቸው?

  • የኪራይ ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ተከራዮችን ከመኖሪያ ቤት የማስወጣት እርምጃዎች በ Seattle ከተማ ውስጥ ለጊዜው ታግደዋል። ይህ እገዳ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ሲሆን እስከ 30 ቀናት ወይም የ Seattle COVID-19 Civil Emergency እስከሚያበቃ ድረስ ይቆያል። 
  • በዚህ ወረርሽኝ ወቅት መሰረታዊ አገልግሎቶች አይቋረጡም። Seattle Public Utilities (SPU፣ ሲያትል የሕዝብ መገልገያዎች) ፣ Seattle City Light (SCL፣ ሲያትል የከተማ መብራት)፣ እና Puget Sound Energy (PSE፣ ፑጂት ሳዉንድ ኢናርጂ)  COVID-19 Civil Emergency በ Seattle ውስጥ በሚተገበርበት ወቅት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። በ COVID-19 ምክንያት የፋይናንስ ጉዳት የደረሰባቸው የ SPU እና SCL ደንበኞች የጀርባ ታሪካቸው ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምንም ቢሆን፣ የክፍያ ማራዘሚያ ዕቅድ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን ይህም የዘገዩ ክፍያዎችን ማስቀልበስን ይጨምራል። በ SPU እና SCL ምክረ ሃሳብ መሰረት፣ ደንበኞች በተቻለ ፍጥነት በስልክ ቁጥር (206) 684-3000 መደወል ወይም በማንኛውም ጊዜ ኢሜይል መላክ አለባቸው፡- seattle.gov/utilities/about-us/email-question። PSE ክፍያቸውን ያዘገዩ ደንበኞች ላይ የሚጠይቀውን ክፍያ ያስቀረ ሲሆን፣ ደንበኞችም ተጨማሪ መረጃ ከ PSE’s COVID-19 Response page ማግኘት ይችላሉ።
  • Utility Discount Program (UDP፣ የመሰረታዊ አገልግሎት የዋጋ ቅናሽ ፕሮግራም) የ Seattle City Light (የሲያትል ከተማ መብራት) ክፍያን በ 60 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን Seattle Public Utility (የሲያትል የሕዝባዊ አገልግሎት) ክፍያን ደግሞ በ50 በመቶ ይቀንሳል። በ UDP ውስጥ ስለመመዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ በስልክ ቁጥር (206) 684-0268 ይደውሉ ወይም ወደዚህ ይግቡ፡ seattle.gov/humanservices/services-and-programs/affordability-and-livability/utility-discount-program
  • የ Seattle ከተማ ይህን COVID-19 (ኮቪድ-19) የሚከተለውንአስጀምሯል፡- የማህበረሰብ መርጃ ገጽ፣ ይህም በየቀኑ የሚሻሻል ነው። ይህ ገጽ በ COVID-19 (ኮቪድ-19) ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ነዋሪዎች የሚያግዙ የ Seattle ከተማ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶችን መረጃና የድረ ገጽ ማስፈንጠሪያዎች የያዘ ነው። እነዚህ የማህበረሰብ መረጃ ምንጮች አብዛኞቹ የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታ መረጃን አይጠይቁም። ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ ይህን ይጎብኙ፡- seattle.gov/covid-19 ወይም በስልክ ቁጥር (206) 684-2489 ወይም (206) 684-CITY ይደውሉ። አስተርጓሚ ይቀርባል። ድጋፍ መስጫ የስልክ መስመር ከሰኞ እስከ አርብ፣ 8:30 AM – 5:00 PM ክፍት ነው።
  • Betancourt Macias Family Scholarship Foundation በሶስት ሰነድ አልባ ጥቁር ሴቶች የተመሰረተና የሚመራ ሲሆን ይህን ስፕሬድሺት የሚያዘምነው እርሱ ነው፡ COVID-19 Resources for Undocumented Communities፣ ይህም ሃገር አቀፍና አካባቢያዊ የመረጃ ምንጮችን የያዘ ነው።

 

6. በወረርሽኙ ምክንያት ስራ አጥ ሆኛለሁ። ለስራ አጥነት ኢንሹራንስ ብቁ ነኝ?

እንደ ሁኔታው ነው። Washington State Employment Security Department (ESD፣ የዋሽንግተን ግዛት የቅጥር ዋስትና መምሪያ) በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተጽእኖ የደረሰባቸውን ሰራተኞች ለማገዝ የተቀረጹ ፕሮግራሞችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ በዚህም ውስጥ የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች ይካተታሉ። ለማመልከት የጸና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ያስፈልግዎታል።

ESD እንዲሁም ለማንበብ ቀላል የሆነ የማነጻጸሪያ መምሪያ ያለው ሲሆን፣ ይህም ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ የተለመዱ ሁኔታዎችና አግባብነት ያላቸውን ጥቅማ ጥቅሞች የሚዘረዝር ነው። ለሰራተኞችና የንግድ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከዚህ ያግኙ፡- esd.wa.gov/newsroom/covid-19። 

 

7. የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅም መቀበል በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዬ ላይ ተጽእኖ ያሳድርብኛል?

የለም። U.S. Citizenship and Immigration Services (የዩኤስ የዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎቶች) ለስደተኛ ሰራተኛ የተከፈሉ የስራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማ ጥቅሞች በሕዝባዊ ክፍያ አወሳሰን ውስጥ ታሳቢ አይደረጉም በማለት በግልጽ አስቀምጧል። የ Washington ግዛት የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅም ኢንሹራንስ ፕሮግራምን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ የፕሮግራሙ ወጪ በዋነኛነት የሚሸፈነው ከአካባቢ ምንጮች ነው።

ለሰራተኞች ተጨማሪ መረጃዎችን ከዚህ ያግኙ፡- esd.wa.gov/newsroom/covid-19። 

 

8. እኔ በመታመሜ ወይም የቤተሰቤ አባል በመታመሙ ወይም በዶክተር መታየት ስላለበት ከስራ እየቀረሁ ነው። ለ Paid Sick & Safe Time (PSST የህመም እና ደህንነት ዕረፍት ጊዜ ክፍያ ለማግኘት) ብቁ ነኝ?

እንደ ሁኔታው ነው። ሁለቱም የ Seattle እና የ Washington ግዛት paid sick እና safe time ህጎች አሰሪዎች እራሳቸውን ወይም የቤተሰብ አባል ወይም የጤና ሁኔታ እንዲጠብቁ ወይም የስራ ቦታቸው፣ የልጅ ት/ቤት፣ ወይም የልጅ እንክብካቤ ቦታ ከጤና ጋር በተገናኘ ምክንያት፣ ለምሳሌ COVID-19፣ ሲዘጋ የክፍያ የእረፍት ጊዜዎችን እንዲሰጡ ያስገድዳሉ።   

የ Seattle PSST ህግ ተግባራዊ የሚሆነው Seattle ውስጥ በሚሰሩ በሁሉም ሰራተኞች ላይ ሲሆን፣ ይህም የዜግነት ወይም የስደተኝነት ሁኔታቸውን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ነው። የ Seattle Office of Labor Standards (OLS) ይህን ህግ በበላይነት የሚመለከት ሲሆን ማናቸውንም ጥሰቶች ይመረምራል። ኦንላይን ቅሬታ ለማቅረብ እና ስለ OLS የሰራተኛ መርጃዎች ይበልጥ ለመማር እዚህ ይጫኑ። ስለ Seattle PSST ድንጋጌ ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎ ወደ Seattle Office of Labor Standards በ (206) 256-5297 ይደውሉ፣ OLS ነፃ የቋንቋ ማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል።

የ Seattle PSST ህግ ተግባራዊ የሚሆነው Seattle ውስጥ በሚሰሩ በሁሉም ሰራተኞች ላይ ሲሆን፣ ይህም የዜግነት ወይም የስደተኝነት ሁኔታቸውን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ነው። የ Washington State Department of Labor & Industries (የሰራተኛ እና ኢንዱስትሪዎች ክፍል) ይህን ህግ በበላይነት ይመለከታል። ለተጨማሪ መረጃ፣ lni.wa.govይጎብኙ።

 

9. እኔ በመታመሜ ወይም የቤተሰቤ አባል በመታመሙ ወይም በዶክተር መታየት ስላለበት ከስራ እየቀረሁ ነው። ለ Washington ግዛት Paid Family and Medical Leave ብቁ ነኝ?

እንደ ሁኔታው ነው። የሚወልዱ፣ ወይም ልጅ በማደጎ የሚያሳድጉ፣ ወይም እራሳቸውን ወይም ሌላን ሰው ለመንከባከብ ጊዜ የሚያስፈልጋቸው ሰራተኞች ለ Washington ግዛት Paid Family and Medical Leave ጥቅሞች ማመልከት ይችላሉ። Washington State Employment Security Department (ESD፣ የዋሽንግተን ግዛት የቅጥር ዋስትና መምሪያ) ይህን ህግ በበላይነት ይመለከታል። ለማመልከት የጸና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ማቅረብ አያስፈልጎትም። ነገር ግን፣ ምናልባት የገንዘብ እርዳታ ወዲያው ላያገኙ ይችላሉ።

የጤና እንክብካቤ አቅራቢው “ከባድ የጤና ሁኔታ” ምክንያት መስራት አለመቻሎን ማረጋገጥ አለበት። በዚህ ፕሮግራም ስር ለይቶ ማቆያ ብቁ ክስተት አይደለም። ነገር ግን፣ አንድ ሰው በ COVID-19 ከታመመ እና የህክምና ማረጋገጫ ማግኘት ከቻለ፣ ለፕሮግራሙ ማመልከት ይችላል። እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል ወደ ሐኪም መሄድ ካልቻለ፣ Employment Security Department (የቅጥር ደህንነት ክፍል) ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ የኤሌክትሮኒክ የህክምና ማረጋገጫ ይቀበላል። የ Seattle ከተማ ESD አዎንታዊ የ COVID-19 ምርመራ ውጤቶችን ከጤና እንክብካቤ አቅራቢ ያለ ማረጋገጫ እንደሚቀበል ለማወቅ በአሁኑ ጊዜ እየሰራ ነው። ለማሻሻያዎች እባክዎ መልሰው እዚህ ይመልከቱ።

ESD እንዲሁም ሁለት የ COVID-19 የሰራተኛ ጥያቄና መልሶችን አዘጋጅቷል፦ ይህኛው ለማንበብ ቀላል የሆነ የማነጻጸሪያ መምሪያ ያለው ሲሆን፣ ይህም ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ የተለመዱ ሁኔታዎችና አግባብነት ያላቸውን ጥቅማ ጥቅሞች የሚዘረዝር ነው።  ይህ ይበልጥ በባህላዊ ጥያቄና መልስ ቅርጸት ነው። ለሰራተኞች ተጨማሪ መረጃዎችን ከዚህ ያግኙ፡ paidleave.wa.gov

 

10. ከሥራ የመቀነስ አደጋ ላይ ካለሁ ወይም እኔ ወይም ወዳጄ በመታመሙ ምክንያት ማቆም ካለብኝስ?

ከአሰሪዎ “standby” የሚባል ነገር መጠየቅ እና ለጊዜያዊ የስራ አጥነት ጥቅሞች ብቁ መሆን ይችላሉ። “Standby” ማለት ስራ ካለማግኘት የተነሳ ለጊዜው ስራ አጥ ነዎት ማለት ሲሆን፣ ነገር ግን ከተለመደው አሰሪዎ ጋር ወደ ስራ በአራት ሳምንታት ውስጥ ይመለሳሉ ወይም የሙሉ-ጊዜ ስራ ከአዲስ አሰሪ ጋር በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይጀምራሉ ወይም በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ለጊዜው ስራ የሎትም ማለት ነው። Washington State Employment Security Department (ESD፣ የዋሽንግተን ግዛት የቅጥር ዋስትና መምሪያ) በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተጽእኖ የደረሰባቸውን ሰራተኞች ለማገዝ የተቀረጹ ፕሮግራሞችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ በዚህም ውስጥ የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች ይካተታሉ። ለማመልከት የጸና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ያስፈልግዎታል።

የ ESD የጉዳይ አስተዳዳሪ ብቁነትን ይወስናል፦ esd.wa.gov/newsroom/covid-19

 

11. የአነስተኛ ንግድ ባለቤት ስሆን በወረርሽኙ ምክንያት የንግድ መቀዛቀዝ እያጋጠመኝ ነው። ለገንዘብ እርዳታ ብቁ ነኝ?

  • ወዲያው የሚደረግ፣ የ Seattle ከተማ Department of Finance and Administrative Services (FAS፣ የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች) ዓመታዊ ተቀራጭ ገቢያቸው $5 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በታች ለሆኑ እና የከተማ ቀረጦችን በሩብ ዓመት ለሚከፍሉ ንግዶች የ business and occupation (B&O፣ ንግድና ሙያ) ቀረጥ መሰብሰቡን አስተላልፏል። ይህ በ COVID-19 (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በተፈጠረው የፋይናንስ ችግር ወቅት የአነስተኛ ንግድ ባለቤቶች ተለዋዋጭነታቸውን እንዲጨምሩ ያደርጋል። ይህ ለሁሉም አነስተኛ ንግድ ባለቤቶች የዜግነት ወይም የስደተኝነት ሁኔታቸው ከግምት ውስጥ ሳይገባ የሚገኝ ነው። ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎ ወደ (206) 684-8484 ይደውሉ ወይም ኢሜይል ያድርጉ፦ tax@seattle.gov
  • City of Seattle Small Business Stabilization Fund (የሲያትል ከተማ የአነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈንድ) ገንዘብ የሚኖር ሲሆን፣ ይህም የድንገተኛ ጊዜ ገንዘብ ሲሆን እስከ $10,000 ድረስ ብቁ ለሆኑ አነስተኛ ንግዶች የመስሪያ ካፒታል ስጦታ ይሰጣል። ይህ ለሁሉም አነስተኛ ንግድ ባለቤቶች የዜግነት ወይም የስደተኝነት ሁኔታቸው ከግምት ውስጥ ሳይገባ የሚገኝ ነው። የብቁነት መስፈርት እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል እዚህ አለ፦ seattle.gov/office-of-economic-development/small-business/small-business-programs-/stabilization-fund-
  • Washington State Employment Security Department (ESD፣ የዋሽንግተን ግዛት የቅጥር ዋስትና መምሪያ) በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተጽእኖ የደረሰባቸውን ሰራተኞች ለማገዝ የተቀረጹ ፕሮግራሞችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ በዚህም ውስጥ የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞች ይካተታሉ። ለማንበብ ቀላል የሆነ የማነጻጸሪያ መምሪያ ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ የተለመዱ ሁኔታዎችና አግባብነት ያላቸውን ጥቅማ ጥቅሞች የሚዘረዝር ነው። ለሰራተኞችና የንግድ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከዚህ ያግኙ፡- esd.wa.gov/newsroom/covid-19
  • የ Seattle ከተማ ይህን COVID-19 አስጀምሯል፦የማህበረሰብ መርጃዎች ገጽ። በየዕለቱ የሚሻሻል ለ አነስተኛ ንግድ/ለትርፍ ያልሆነ ድጋፍ የሆነ ክፍል ይዟል። እነዚህ የማህበረሰብ መረጃ ምንጮች አብዛኞቹ የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታ መረጃን አይጠይቁም። ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ ይህን ይጎብኙ፡- seattle.gov/covid-19 ወይም በስልክ ቁጥር (206) 684-2489 ወይም (206) 684-CITY ይደውሉ። አስተርጓሚ ይቀርባል። ድጋፍ መስጫ የስልክ መስመር ከሰኞ እስከ አርብ፣ 8:30 AM – 5:00 PM ክፍት ነው።
  • ተጨማሪ እገዛ ሊመጣ ይችላል። የ Seattle ከንቲባ Jenny Durkan Small Business Recovery Task Force ያቋቋሙ ሲሆን፣ ይህም የረጅም-ጊዜ የፖሊሲ ጥቆማዎችን የሚመክር እና ቴክኒካል እገዛ እና ስርጭት በዚህ ወረርሽኝ ለተጎዱ አነስተኛ ንግዶች ይሰጣል።

 

12. ለ Seattle ከተማ አነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈቃድ ወይም ለፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር አደጋ ብድር ማመልከት በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታዬ ላይ ተጽእኖ ያሳድርብኛል?

የለም። ለ Seattle ከተማ አነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈቃድ ወይም ለፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር አደጋ ብድር ማመልከት በአዲሱ የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ለዜግነት የማመልከት ችሎታ ላይ ተጽእኖ አያሳድርቦትም። የ Seattle ከተማ አነስተኛ ንግድ ማረጋጊያ ፈቃድ አካባቢያዊ የከተማ ደረጃ ፈቃድ ነው። እና በአካባቢው ያሉ በቅናሽ ዋጋ የሕክምና እንክብካቤ የሚሰጡ ፕሮግራሞች አሁን ባለው የሕዝባዊ ክፍያ ደንብ መሰረት እንደ ሕዝባዊ ጥቅም አልተዘረዘሩም። ፌዴራል አነስተኛ ንግድ አስተዳደር አደጋ ብድር የአደጋ እፎይታ ነው ተብሎ ይታሰባል። እነዚህ የአደጋ እፎይታ ፕሮግራሞች በሕዝባዊ ክፍያ ደንብ አልተካተቱም። በአዲሱ ሕዝባዊ ክፍያ ፖሊሲ ስር ለተካተቱ የሕዝባዊ ጥቅም ፕሮግራሞች ዝርዝር እባክዎ ጥያቄ 3 ይመልከቱ።

 

13. ለበለጠ መረጃ መርጃዎች፦

ለበለጡ ጥያቄዎች እባክዎ ለ Joaquin Uy በ joaquin.uy@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ።